A few of my ግጥምs
June 14, 2019 at 3:18 pm Leave a comment
Here, kids, is my first Amharic poem at least a decade after I stopped writing in the mother-tongue. It is dedicated to Facebook, and all those whose hearts are unsettled. Who, like Oliver, can’t help but ask for [and wonder if there was not] more. To those for whom “enuff” is never enough. [That is Qine, right there. Give it time ;)].
ልቤ ሸርሙጣ ነው
ኩታራ መናኛ
‘ፍቅር’ ካላቀፈ
አርፎ የማይተኛ::
ምሽት ጠብቆ አዳኝ
ተግዋዥ በጨረቃ
ተቅበዝባዥ
ተልከስካሽ
“Connection” ፍለጋ
[“Acceptance” ፍለጋ]
[መሳይ-ነብሥ ፍለጋ]::
ያመኑትን ከጂ
ያጎረሰን ነካሽ
[ልቤ ሸርሙጣ ነው]
መንገድ ዉሎ አዳሪ
ተለዋጭ
ተገልባጭ
ተበራዥ
ተከላሽ::
A poem I wrote in my early 20s [to a “bird” who turned out to be a fish :)].
አታባብለኝ
አታባብለኝ
– ላትሆነኝ
በኛ መሃል
… ላይዘልቅ ፍቅር
አበቃቀላችን
– ለየቅል!
አታባብለኝ
– አትደልለኝ
ልቤን በከንቱ አታስነሳ…
የት ልንኖር፣
– ቢሆን እንኩዋ
እኔ እና አንተ
– ወፍና ዓሣ!
This last, and least, poem I wrote on June 11, 2020 @ 11:09.
እኔ ሳድን
አንተ ስትድን
ተሙለጭልጨህ ስታመልጠኝ
“Ignore button” እየተጫንክ
እንዳልቀረበ ስትርቀኝ::
እንዳይን ስትጠፋ
– እልም ብለህ
ግድ ሳይልህ
የኔ ጥቃት
[የኔ ጭንቀት
የኔ ናፍቆት]
ምን ተገኘና ዛሬ
አሳሰበህ በር መምታት?
[ሂድ…]
አሳዳጅህ አይደለሁም
ለቅቄያለሁ ያንን ስፍራ
ሌላ ገልቱ ትኑርበት
አልበገር-ባይ ልብህን
– ትስበር.. ታልምድ..
ትግዛ..
ትግራ::
እስክትጀምር ጨዋታህን
“አየሁሽ”ህ ትክ እስኪላት
ግፋ.. ቀጥል..
በርታ.. ጀግን..
[የኔ ንፋስ፣ የኔ ላጲስ
የኛ’ ንቦቃቅላ ንጉሥ]
የሆንክልኝን ሁሉ ሁንላት!
መታሰቢያነቱ:- እድሜ ለማያበስላቸው ያገሬ ወንዶች
ወፌ ላላ
ወፌ ላላ
ወፌ ላላን..
– ልበላ
ወጥመድ አጥምጀ
– ደጄ..
የፀሐይ ወበቅ
– ሙቀት..
አንቀላፍቶኝ
– አለሁበት
ወፌ ላላ
– መጥታ..
ስጤን
– በልታ
በርራ ሄዳ
ኖሮዋል ለካ
ወ-ጥ-መ-ዴ-ን
ሳትነካ!
– ለፍቀርተ
Entry filed under: Latest Posts.
Trackback this post | Subscribe to the comments via RSS Feed