On Hachalu…
July 3, 2020 at 3:54 am Leave a comment
የ-ሞ-ተ-ስ….
አረፈ
ከጣድቃን መካከል
ስሙ ተሰለፈ
ደግ ደጉ ተመርጦ
ስራው ተነገረ
[ጀብዱ ተተረከ]
በታሸ ብራና
በተሳለ ብዕር
በወርቅ-ቅብ ተፃፈ::
ኗሪ ነው የዋሁ
የግዜር በግ ተላላ
ለመቃብር… ድንጋይ
ለአስለቃሽ… ለሰልስት
ለንፍሮ… ሙታ’መት
[“ለስሙ” … “ለክብሩ”
ለቤቱ… ላገሩ
ለጭዱ… ለሣሩ
ለቅጠል… ላፈሩ]
ፍዳ የሚበላ!
ተፃፈ: July 2nd, 2020 @ 5:41 pm

Entry filed under: Latest Posts.
Trackback this post | Subscribe to the comments via RSS Feed