ሆድ ሲብሰኝ…
October 15, 2020 at 12:33 am Leave a comment
እግዜር የለም
እናት ዓለም
“እግዜር አለ” አትበይኝ
ተሞኝተሽ አታሞኝኝ
እግዜር ካለ-
የዱለኞች ጠበቃ ነው
የክፉ ሰው አቡካቶ
ፊቱን መላሽ
ባመፅ ፈራጅ
ደሃ ሲበደል አይቶ
ላለው ወዳጅ
አጎብግዋቢ
ጉልበት, ገንዘብ,
ብሔር, ቀለም,
እግዜር ካለ
[ፍቺኝ እማ]
ከከሳሹ ጎን ልጠራ
ከጠሉት ወገን ልመደብ!
Entry filed under: Latest Posts.
Trackback this post | Subscribe to the comments via RSS Feed